ስለ ሮክስ (Roks)

ስለ ሮክስ (Roks)

ስለ ሮክስ

 ሮክስ በስዊድን የሚገኝ ብሄራዊ የሴቶችና ወጣት ሴቶች መጠለያ ድርጅት ነው። በሀገሪቱ ወስጥ ከሚገኙት ትልቁየሴቶችና ወጣት ሴቶች መጠለያ ነው፡፡ የሮክስ አላማዎች በመጠለያው በጋራ ፍላጎቶች አማካኝነት በሴቶች ላይለሚደርሰው የወንዶች ጥቃት እንዳይደርስ ጥበቃ ለማድረግ ነው፡፡ ሮክስ ሕዝባዊ ሀሳቦችን ይቀርጻል። መጠለያውየሚጋፈጣቸውን ነገሮች ለህዝብ ያሳውቃል፥ መጠለያውን የሚመለከቱ ጉዳዮችን ይመረምራል፡፡ አሁን በድርጅቱ 100 የሚጠጉ ሴቶችና ወጣት ሴቶች ይገኛሉ፡፡ ሮክስ በሴቶች ጉዳይ ላይ የሚንቀሳቀስ ድርጅት ሲሆን ተግባሩም በሴቶችናወጣት ሴቶች መብቶችና ነጻነት ላይ እንዲሁም በሁሉም የእኩልነት ደረጃ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

 

የሴቶቹ መጠለያዎች

እያንዳንዱ መጠለያ ራሱን የቻለና በራሱ መንገድ የሚሰራ ነው፡፡ ያም ሆኖ ሁሉም መጠለያዎች ሴቶችና ወጣት ሴቶችእርዳታ ሲፈልጉ የድንገተኛ እርዳታ ስልክ ጥሪ ማድረግ የሚችሉበት የስልክ መስመር አለ፡፡ ደዋዮች ማንነታቸውን ለመግለጽ አይገደዱም። የደወለም አይመዘገብም፡፡

የሴቶቹ መጠለያ የተገልጋዮችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ድጋፍ ይሰጣል፡፡ ምን አልባት ስላለችበት ሁኔታና ስለ ግንኙነትልታወራ ትችላለች፡፡ ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ ወይም የአሳዳጊነት ሙግት ምክር ልትፈልግ ትችላለች፡፡ አሁን ወይም ከብዙአመታት በፊት የጾታ ጥቃት የደረሰባት ልትሆን ትችላለች፡፡ ለዚህም በመጠለያው የሚሰሩ ሴቶች ድጋፍና ምክሮችንይለግሳሉ። ለምሳሌ ወደ ፖሊስ፣ ወደ ጠበቃና ወደ ማህበራዊ አገልግሎት ሰጪዎች መሄድን በተመለከተ ድጋፍያደርጋሉ፡፡ አብዛኛዎቹ መጠለያዎች ለባለጉዳይ ሴቶቹና ለልጆቻቸው መጠለያ ያቀርባሉ፡፡

ብዛት ያላቸው መጠለያዎች ህጋዊ ሆስቴል ተብለው ተለያይተዋል፡፡ ጥቂት መጠለያዎች የመስማት ችግር ላለባቸውሴቶች የጽሁፍ ስልክ መጠቀሚያ አላቸው፡፡ ሌሎች መጠለያዎች ከቅርብ ዘመድ ጋር ስለተደረጉ ጾታዊ ግንኙነቶችበተመለከተ ለማስተናገድ ተብለው በልዩ ሁኔታ የተዘጋጁ ናቸው፡፡ 

የሴቶች መጠለያን እዚህ ጋር ያግኙ

 

የወጣት ሴቶች መጠለያ

በሮክስ 30 ያህል የወጣት ሴቶች መጠለያዎች ሲኖሩ ከነዚህ ውስጥም አስር ያህሉ ገለልተኛ ድርጅቶች ናቸው፡፡ የወጣትሴቶች መጠለያው ልክ እንደ ሴቶች መጠለያው በተመሳሳይ መንገድ የሚሰራ ሆኖ ነገር ግን ለወጣት ሴቶች የተባለሲሆን ለምሳሌ ማስፈራራት፣ ማጎሳቆልና የፆታ ጥቃትን ወይም በሌላ ምክንያት፣ ሌሎች ልጃገረዶችን ማነጋገርንበተመለከተ ይሰራል፡፡ እንዲሁም ልጃገረዶቹ በመጠለያው የሚገኙበትን ሁኔታ ለህዝብ ግንዛቤ ለማስጨበጥ በንቃትይሰራል፡፡ የወጣት ሴቶቹ መጠለያዎች ድረገጽ  አላቸው፡፡ ይህም የሚከተለው ነው። www.rokstjejjourer.se

የወጣት ሴቶችን መጠለያ እዚህ ጋር ያግኙ

 

በመጠለያው መስራት

በመጠለያው የሚሰሩ አብዛኞቹ የበጎ ፈቃድ አገልጋዮች ናቸው፡፡ በመጠለያው ተቀባይነትን ለማግኘት መጀመሪያበመጠለያው በሚዘጋጀው የጥናት ክበብ ላይ መሳተፍ ያስፈልጋል፡፡ የሰራተኛ አባል ለመሆን ከፈለጉ በአካባቢዎየሚገኘውን የሴቶች ወይም ልጃገረዶች መጠለያ ያግኙ፡፡